Fana: At a Speed of Life!

ለፓርቲው ውሳኔዎች ስኬታማነት የህዝቡ ድጋፍ ሊጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፓርቲው ውሳኔዎች የብልጽግናን ጉዞ የሚያሳኩ በመሆናቸው ህዝቡ ድጋፉን ሊያጠናክር እንደሚገባው ተገለፀ።

 

በደብረ ብርሃን ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የህዝብ ኮንፈረንስ የተሳተፉት በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ከፍያለው ተፈራ÷ በሀገራዊ ለውጡ የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማጠናከር ትኩረት ተደርጓል ብለዋል።

 

በተለይም በበጋ መስኖ ስንዴ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ፣ በኮሪደር ልማትና በሌሎች የልማት ስራዎች ላይ የተመዘገቡ ስኬቶች እንደሚጠናከሩ ገልጸዋል።

 

የተገኙ ስኬቶች የብልጽግና ጉዞን በማሳለጥና ሀገራዊ ዕድገትን ዳር ለማድረስ የሚያስችሉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

 

በብልጽግና ፓርቲ የሲዳማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አብርሃም ማርሻሎ በበኩላቸው÷ የፓርቲው ውሳኔዎች ዘላቂ ዕደገት ለማስመዝገብ የሚያስችሉ መሆናቸውን አንስተዋል።

 

በተለይም የጋራ ትርክትን በማጎልበትና የተቋማት ግንባታን በማጠናከር ረገድ ህዝቡ ከፓርቲው ጎን በመሆን በንቃት እንዲሳተፍ መግለጻቸውን ኢዘአ ዘግቧል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.