አትሌት ሰለሞን ባረጋ የሲቪያ ማራቶንን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አትሌት ሰለሞን ባረጋ በስፔን ሲቪያ በተካሄደው የማራቶን ውድድር አሸንፏል፡፡
አትሌት ሰለሞን 2 ሰዓት ከ5 ደቂቃ ከ14 ሰከንድ በመግባት ነው የማራቶን ውድድሩን ያሸነፈው፡፡
አትሌት ሰለሞን ባረጋ የማራቶን ውድድሩን ለመጀመሪያ ጊዜ ማድረጉንም የኢትዮጵያ አቲሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡