Fana: At a Speed of Life!

129ኛው የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል’’ በሚል መሪ ኃሳብ ይከበራል

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 129ኛዉ የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል’’ በሚል መሪ ኃሳብ እንደሚከበር የመከላከያ ሰራዊት አስታወቀ፡፡

አከባበሩን በሚመለከት የመከላከያ ስነ ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜ/ጀነራል እንዳልካቸው ወ/ኪዳን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸው የዓድዋ ድል የኢትዮጵያ ብቻ አይደለም፤ የመላ አፍሪካዊያን ነው ያሉ ሲሆን ዘንድሮ” ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል ’’ በሚል መሪ ኃሳብ እንደሚከበር ገልጸው፤ በዓሉን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ኮሚቴ ተቋቁሞ ዝግጅት መደረጉን አንስተዋል፡፡

ከበዓሉ ቀደም ብሎም በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም በኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ሚሲዮኖች ጭምር እንደሚከበር ጠቁመዋል።

ዓድዋ የጋራ ድል፣ የአንድነት፣ የአላማ ፅናት እንዲሁም የአሸናፊነት ምሳሌ በመሆኑ የአባቶችን አርበኝነት በመያዝ ዘመኑ የሚጠብቅብንን ኃላፊነት መወጣት አለብን ሲሉ ሜ/ጀ እንዳልካቸዉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በሰለሞን በየነ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.