Fana: At a Speed of Life!

ከ254 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከየካቲት 7 እስከ 13 ቀን 2017 ዓ.ም 254 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ዋጋ ያላቸው የገቢ እና ወጪ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን ጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በተጨማሪም የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 17 ተጠርጣሪ ግለሰቦች እና ስምንት ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገልጿል፡፡

ከተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል፤ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ ጥራጥሬ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ ዕቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች ፣ መድኃኒት፣ የቁም እንስሳት እና የውጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የገቢ እና የወጭ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር አዲስ አበባ ኤርፖርት፣ ሞያሌ እና አዳማ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ መባሉን የኮሚሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.