Fana: At a Speed of Life!

83 መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰተኞች ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 83 መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰተኞች ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ገለጹ፡፡

በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከዓለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም ጋር በመተባበር ፍልሰተኞቹ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ማድረጋቸውን አምባሳደሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ መርሆችን በማክበር ድንበር ዘለል ወንጀሎችን እንደምትከላከል ጠቅሰው፤ ፍልሰተኞች ሕጋዊ በሆነ መንገድ ብቻ ከሀገር ወደ ሌላ ሀገር መንቀሳቀስ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.