Fana: At a Speed of Life!

የአዋሽ ተፋሰስን ደህንነት በማስጠበቅ የአረንጓዴ ልማትን መደገፍ የሚያስችል ስምምነት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአዋሽ ተፋሰስን ደህንነት በማስጠበቅ የአረንጓዴ ልማትን መደገፍ የሚያስችል ስምምነት ከኔዘርላድስ የውሃ ባለስልጣን ጋር አድርጓል፡፡

በአዋሽ ተፋሰስ ላይ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከኦሮሚያ፣ ከአማራና አፋር ክልሎች ጋር በውሃ ጥራት፣ በውሃ ምደባና በጎርፍ መከላከል ዙሪያ የትብብር ማዕቀፍ በማዘጋጀትና ስምምነት በመውሰድ ሲሰሩ እንደቆዩ ተመላክቷል፡፡

የኔዘርላንድስ መንግስት የውሃ ባለስልጣን በአዋሽ ተፋሰስ ላይ የተሻለ የውሃ አቅርቦት እና ጥራት እንዲኖር፣ የአረንጓዴ ልማትን በማጠናከር፣ የጎርፍ አደጋ መከላከል ላይ የሚሰራውን ስራ ለመደገፍ ስምምነት አድርጓል።

ፕሮጀክቱ ተፈጥሮን መሠረት ያደረጉ መፍትሄዎችን በመውሰድ የውሃ አቅርቦትን ለማሻሻል የውሃ ምንጮችን እና በተፋሰስሱ ውስጥ ያሉ መሠረተ ልማቶችን መጠበቅ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡

የተፋሰሱ ተጋሪ በሆኑ ክልሎች ላይም ፕሮጀክቱ እንደሚተገበር የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.