Fana: At a Speed of Life!

በ150 ሚሊየን ብር የተገነባው የዘይት ፋብሪካ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ በ150 ሚሊየን ብር የተገነባው የዘይት ፋብሪካ ተመርቋል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሀሰን በዚሁ ወቅት፤ በክልሉ በተለይም ለዘይት ፋብሪካ ግብዓት የሚሆኑ ምርቶች በስፋት እንደሚመረቱ ጠቅሰዋል፡፡

ፋብሪካው የሕብረተሰቡን የዘይት ፍላጎት በመመለስ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚያበረክት በመግለጽ፤ ለአልሚ ባለሃብቶች የሚደረገው ድጋፍ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

በፋብሪካው የምረቃ-ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በበኩላቸው፤ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለውን ዐቅም በኢንዱስትሪ ለመደገፍ እየተደረገ ያለውን ጥረት በማጠናከር የበለጠ ውጤታማ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

የፋብሪካዎች መበራከት በክልሉ የሚገኙ የማዕድንና የግብርና ምርቶችን በኢንዱስትሪ ውስጥ አልፈው ለክልሉም ሆነ ለሀገር እንዲጠቅሙ ያስችላል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.