ያለ ፀሐይ ብርሃን መንቀሳቀስ የማይችሉ ወንድማማቾች
ሹዊብ እና አብዱልረሽድ በደቡብ ምዕራብ ፓኪስታን ፓሎጂስቲያን ግዛት ገጠራማ መንደር የሚኖሩ ሁለት ወንድማማቾች ናቸው።
ሹዊብ የ13 ዓመት ራሽድ ደግሞ የ12 ዓመት ታዳጊዎች ሲሆኑ÷ ሁለቱ ወንድማማቾች ተፈጥሯቸው ከሌሎች ልጆች ለየት ያለ ነው።
ከእኩዮቻቸው ጋር ጨዋታ ላይ ቢሆኑም እንኳ ፀሐይ ማዘቅዘቅ ስትጀምር ወደ ቤታቸው እንዲገቡ ቤተሰቦቻቸው ያስገድዳቸዋል። ምክንያቱም ፀሐይ አዘቀዝቃ ወደ ማደሪያዋ ስትወርድ የሁለቱ ወንድማማቾች ሰውነት ይዝላል፣ ሰውነት ይከዳቸዋል፣ አቅም ያንሳቸዋል።
የልጆቹ ወላጅ አባት የሆኑት ሀሽም ስለ ልጆቻቸው በሰጡት አስተያየት እንዳሉት÷ ቀን ቀን ይጫወታሉ ነገር ግን ምሽቱ ሲጀምር ሰውነታቸው ይደክማል። በዚህም ምክንያት ከቤት ሲወጡ ስጋት ውስጥ እገባለሁ፤ ከሰዓት ልክ እንደ እኩለ ሌሊት እነሱን ፍለጋ እወጣለሁ ፀሐይ ከገባች አንድ ነገር ይሆናሉ ብለን እንሰጋለን ብለዋል።
መጀመሪያ አካባቢ በልጅነታቸው ደካማ ሆነው ነበር የታዩኝ እድሜያቸው እየጨመረ ሲሄድ ግን ጉዳዩ አሳሳቢ እየሆነ መጣ የሚሉት አባታቸው÷ ወደ ሆስፒታል በተደጋጋሚ ወስጃቸዋለሁ ነገር ግን ሀኪሞች ችግራቸው ምን እንደሆነ ሊረዱ አልቻሉም ሲሉም አክለዋል።
ፀሐይ ስትገባ የራሺድና ሹዊብ ሰውነት እንደ ቀኑ አይሆንም ሰውነታቸው ያለ ፀሐይ አይሰራም።
ታዳጊዎቹ ፀሐይ ስትገባ ሰውነታችን ይጎዳል፣ እግራችንም ይደርቃል፣ መንጋጋችን ይዘጋል፣ ጥርሳችንም ይቆለፋል፣ ፀሐይ ስትገባ ምሽታችን ከባድ ነው ምንም ማድረግ አንችልም ሲሉም የሚሰማቸውን ስሜት ይገልፃል፡፡
ፀሐይ ስትፈነጥቅ የወንድማማቾቹ ሰውነት ከመቆላለፍ ተላቆ መሥራት መንቀሳቀስ ይጀምራል።