Fana: At a Speed of Life!

ተግዳሮቶችን ለመፍታት የተሻሻለ የዓለም አቀፍ ሥርዓት ያስፈልጋል – ማሞ ምህረቱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በብራዚል ብራዚሊያ በተካሄደው የመጀመሪያው የ2025 የብሪክስ ሼርፓስ ስብሰባ ተካፍሏል።
ማሞ ምህረቱ በመድረኩ እንዳለመከቱት፤ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት የባለብዙ ወገንተኝነት እና የጋራ ደህንነት ስርዓት ለረዥም ጊዜ ስትደግፍ ቆይታለች።
በርካታ እና ውስብስብ የሆነውን የዓለም አቀፍ ተግዳሮት ለመፍታት የተሻሻለ የዓለም አቀፍ ሥርዓት እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።
የአዲሱ ልማት ባንክ አባል መሆን በፈረንጆቹ 2025 የኢትዮጵያ ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫዎች መካከል አንዱ መሆኑንም ገልጸው፤ በብሪክስ መድረክ ውስጥ ያሉትን ዋና ዓላማዎችን፣ መርሐ-ግብሮችን እና ዕቅዶችን ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።
በጉባዔው የዓለም ዓቀፍ ጤና፣ የዓለም አቀፍ አስተዳደር ማሻሻያ፣ የአየር ንብረት ፋይናንስ፣ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አስተዳደር እና የዓለም ደቡብ ትብብር እንዲሁም የብሪክስ ተቋማዊ እድገት ኢትዮጵያ ትኩረት የምትሰጣቸው ቁልፍ ጉዳዮች እንደሆኑም ተገልጿል።
በብራዚል የተጀመረው ጉባዔ ለሁለት ቀናት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ መወያየቱን እንደሚቀጥል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.