በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ምሽት ሊቨርፑል ከኒውካስል ዩናይትድ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ27ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በዋንጫ ፉክክሩ ላይ ወሳኝነት ያላቸው ተጠባቂ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይከናወናሉ።
የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ምሽት 5 ሰዓት ከ15 የቀጣይ ዓመት የሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎን ለማግኘት የሚፋለመውን ኒውካስል ዩናይትድ በአንፊልድ ያስተናግዳል።
ከዚህ ጨዋታ ቀደም ብሎ ምሽት 4:30 ላይ በደረጃ ሰንጠረዡ 2ኛ ላይ የሚገኘው አርሰናል ከተከታዩ ኖቲንግሃም ፎረስት ጋር ከሜዳው ውጭ የሚያደርገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
ማንቼስተር ዩናይትድ ከኢፕስዊች ታውን፣ ብሬንትፎርድ ከኤቨርተን እንዲሁም ማንቼስተር ሲቲ ከሜዳው ውጭ ከቶተንሃም ጋር በተመሳሳይ ምሽት 4 ሰዓት ከ30 ይገናኛሉ።
ትናንት በተከናወነው የ27ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር ቼልሲ ሳውዛምፕተንን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ አራተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።
በተመሳሳይ ብራይተን ቦርንማውዝን እንዲሁም ፉልሃም ወልቭስን 2 ለ 1 ፥ ክሪስታል ፓላስ አስቶንቪላን 4 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል፡፡