Fana: At a Speed of Life!

ኢጋድ የሴቶች ዐቅም የማጎልበት ሥራን እንደሚያጠናክር አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት (ኢጋድ) የሴቶችን ዐቅም የማጎልበት ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የተቋሙ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡

ዋና ፀሐፊው በተቋሙ በተዘጋጀ የሴቶች ዐቅም ግንባታ ሥልጠና ላይ ተገኝተው ማበረታታቸውን በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

ሴቶችን በተመለከተ የሚስተዋሉ ዘመኑን ያልዋጁ አመለካከቶችን ጨምሮ የማኅበራዊ መዋቅሮች ችግሮች ሴቶች ስኬታማ እንዳይሆኑ ተግዳሮት እየሆኑ ነው ብለዋል፡፡

ኢጋድ እስከ ፈረንጆቹ 2030 የሥርዓተ ጾታ እኩልነትን ለማረጋገጥ እያከናወናቸው ባሉ ተግባራት ውጤቶች ቢታዩም፤ አሁንም የሥርዓተ ጾታ እኩልነትን በተመለከተ ችግሮች መኖራቸውን አንስተዋል፡፡

ሴቶች በሁሉም ዘርፍ ስኬታማ እንዲሆኑ ዐቅማቸውን ማጎልበት እንደሚገባ አስገንዝበው፤ ኢጋድ ቀጣይነት ባለው መልኩ ሴቶችን የመደገፍ ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.