የብሪክስ ሼርፓስ ስብሰባ ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በብራዚል ብራዚሊያ በተካሄደው የ2025 የመጀመሪያው የብሪክስ ሼርፓስ ስብሰባ ተጠናቅቋል፡፡
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በስብሰባው መካፈሉ ይታወቃል፡፡
የብራዚል ፕሬዚዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ ብራዚል ቅድሚያ የምትሰጣቸው በዓለም አቀፍ የጤና ትብብር፣ አካታች አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አስተዳደር፣ የተሻሻለው የዓለም ኢኮኖሚ እና ፋይናንሺያል አርክቴክቸር፣ ውጤታማ የአየር ንብረት ፋይናንስ አርክቴክቸር፣ የተሻሻለ የግሎባል ደቡብ ትብብር እና ጠንካራ ተቋማዊ እድገትን እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡
የብሪክስ ሀገራት የተባበሩት መንግስታትን ማዕከል ያደረገ ባለ-ብዙ ወገንተኝነትን የማሳደግ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል።
በስብሰባው ኢትዮጵያ ለባለብዙ ወገን፣ ለጋራ ደህንነት እና ለዘላቂ ልማት ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጣለች።