አየር መንገዱ ወደ ፖርቶ ከተማ የበረራ አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፖርቱጋል ፖርቶ ከተማ በሳምንት አራት ቀን የበረራ አገልግሎት መስጠት ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ።
አየር መንገዱ ወደ ከተማዋ ከሀምሌ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሳምንት አራት ቀን የበረራ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ወደ አውሮፓ ለሚጓዙ መንገደኞች የተቀላጠፈና ምቹ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችለው ገልጿል።
የበረራው መጀመር አየር መንገዱ በአውሮፓ ሀገራት ያለውን የበረራ አድማስ እንደሚያሳድግለትም አመልክቷል።