Fana: At a Speed of Life!

የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አመራር ዐቢይ ኮሚቴ አራተኛ መደበኛ ስብሰባ አካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አመራር ዐቢይ ኮሚቴ አራተኛ መደበኛ ስብሰባ ማካሄዱን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ በስብሰባው የመንግስት አገልግሎት ለተገልጋይ ቀላል፣ ግልፅ፣ በቴክኖሎጅ የታገዘ ቀልጣፋ እና በአንድ ማዕከል ማቅረብ የምንችልበትን ህጋዊ አሰራር ለመዘርጋት በሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች ዙሪያ መክረናል ብለዋል።

በመሆኑም የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎትን ለማቋቋም የሚያስችል ህጋዊ የአሰራር ስርዓት ሰነድ ላይ በመወያየት አሰራሩን ጠብቆ ፀድቆ ወደ ተግባር እንዲገባ ወስነናል ሲሉ አመልክተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.