ወላይታ ድቻ ኢትዮዽያ መድንን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ20ኛ ሳምንት የኢትዮዽያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ወላይታ ድቻ የሊጉን መሪ ኢትዮጵያ መድንን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
የወላይታ ድቻን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ በመጀመሪያው አጋማሽ ፀጋዬ ብርሃኑ አስቆጥሯል።
በአሰልጣኝ ገብረ መድን ኃይሌ የሚመሩት መድኖች ከተከታያቸው ሀዲያ ሆሳዕና ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ 7 ከፍ ማድረግ የሚችሉበትን እድል ሳይጠቀሙ ቀርተዋል።
የሊጉ ጨዋታ ቀጥሎ ሲደረግ ምሽት 12 ሰዓት ላይ አርባ ምንጭ ከተማ ከፋሲል ከነማ ይገናኛሉ።