Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለዕይታ ቀረቡ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል በተዘጋጀው ዐውደ ርዕይ ምርትና አገልግሎቶቹን ለዕይታ አቅርቧል።

በዐውደ ርዕዩ ላይ የሮቦቲክስ እና የሆሎግራም ቴክኖሎጂ እንዲሁም በኢንስቲትዩቱ የበለፀጉ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ውጤት የሆኑ መተግበሪያዎች ለዕይታ ቀርበዋል፡፡

የተለያዩ ተቋማት ምርትና አገልግሎቶቻቸውን የሚያሳዩበት ዐውደ ርዕይ ለተከታታይ 10 ቀናት ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ እንደሚቆይም ከኢንስቲትዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ማዕከሉ በትላንትናው ዕለት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተመርቆ መከፈቱ ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.