Fana: At a Speed of Life!

129ኛው የዓድዋ ድል በዓል በመላ ሀገሪቱ ተከብሮ ዋለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 129ኛው የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል” በሚል መሪ ሀሳብ በሀገር አቀፍ ደረጃ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተከብሯል።

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በዓሉን በማስመልከት ዛሬ ማለዳ በዳግማዊ ምኒልክ ሐውልት ስር እንዲሁም በዓድዋ መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል፡፡

በዓሉ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ፕሬዚዳንቱን ጨምሮ የህዝብ ተወካዮችና የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች እንዲሁም የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች በተገኙበት ተከብሯል፡፡

ዓድዋ ከኢትዮጵያ ባለፈ የመላው ጥቁር ህዝቦች ድል መሆኑ በክብረ በዓሉ ላይ የተነሳ ሲሆን፤ ኢትዮጵያዊያን ለድሉ መሰረት የነበረውን አንድነትና ጽናት በመውረስ በልማት መድገም እንዳለባቸው ተጠቁሟል፡፡

በዓሉ በመላ ሀገሪቱ እንዲሁም በተለያዩ ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽህፈት ቤቶች በዓሉን በሚዘክሩ የተለያዩ ሁነቶች ተከብሮ ውሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.