በጃፓን በተቀሰቀሰው የሰደድ እሳት ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቀሉ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጃፓን የተከሰተው ሰደድ እሳት በግማሽ ክፍል ዘመን ታይቶ የማይታወቅና ለመቆጣጠር አስቸጋሪ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ሰደድ እሳቱን ለማጥፋት 2 ሺህ የሚሆኑ የአየር እና የምድር የእሳት አደጋ ሰራተኞች ጥረት እያደረጉ ቢሆንም÷ ለመቆጣጠር አዳጋች እንደሆነባቸው ተነግሯል፡፡
በሀገሪቱ ሰሜን ምስራቅ በተከሰተው ሰደድ እሳት እስካሁን የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ፤ 4 ሺህ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፡፡
በሰደድ እሳቱ 80 ህንጻዎች መውደማቸው የተገለጸ ሲሆን፣ 2 ሺህ 600 ሄክታር መሬት የሚሆን ከባቢን ማውደሙም ተጠቁሟል፡፡
ጃፓን በፈረንጆቹ 1975 ሆካይዶ በሚባለው አካባቢ 2 ሺህ 700 ሄክታር መሬት በሰደድ እሳት ከወደመባት ወዲህ ይህ የመጀመሪያው አስከፊ ሰደድ እሳት መሆኑንም የኤሲያ ፓስፊክ ዘገባ አመላክቷል፡፡
በአቤል ንዋይ