Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ሥርዓት ወደ ብዝኃ-መር መቀየር አለበት – ቻይና

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም ሥርዓት ከአንድ ብቻ መር ወደ ብዝኃ-መር መቀየር እንዳለበት ቻይና አስገነዘበች፡፡

የሀገሪቱ ከፍተኛ ምክር ቤት ዓመታዊ ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል።

በዚሁ ወቅት የቻይና ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ እንዳሉት፤ ሀገራቸው የተሻለ ዓለም ለመፍጠር ከሀገራት ጋር ትብብሯን እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

ቻይና የተሻለ ሥርዓት ለመፍጠርና የሁሉንም ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደምትሠራ ገልጸው፤ ለዚህም የዓለም ሥርዓት ከአንድ ብቻ መር ወደ ብዝኃ-መር መቀየር እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

በሕዝቦች መካከል እኩልነትና መተባበር እንዲኖር የተጀመሩ ሥራዎች እንደሚቀጥሉም አመላክተዋል፡፡

ሁሉን ጠቃሚ እና ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ሉላዊነት፣ የዓለም አቀፍ ልማት ኢኒሼቲቭን ማሳደግ፣ የዓለም አቀፍ ደኅንነት ተነሳሽነት መጨመርና የዓለም የአሥተዳደር ሥርዓት ማሻሻያ ሊተኮርበት ይገባል ነው ያሉት።

ለዚህም ቻይና ከቪዛና ከታሪፍ ነፃ አሠራሮችን መተግበር መጀመሯን አስታውቀው፤ ‘ቤልት ኤንድ ሮድ’ እና ሌሎች የድጋፍ ማዕቀፎችም እንደሚቀጥሉ ማረጋገጣቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

ቻይና የ6ኛው ትውልድ ቴክኖሎጂን ማበልፀግና የሰው ሠራሽ አስተውሎትን በቀጣዩ ዓመት የመሥራት ዕቅዷንም አስተዋውቃለች።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.