የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ሴት ነጋዴዎች የንግድ ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 6ኛው የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) ሴት ነጋዴዎች ፌዴሬሽን የንግድ ኤግዚቢሽንና ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴዔታ ያስሚን ወሀብረቢ የንግድ ኤግዚቢሽንና ኮንፈረንሱን አስመልከቶ ከፌዴሬሽኑ ቦርድ ሰብሳቢ ማውሪን ሱምብዌ ጋር ተወያይተዋል፡፡
የንግድ ኤግዜቢሽንና ኮንፈረንሱ ለኢትዮጵያና ለኮሜሳ አባል ሀገራት ሴት ነጋዴዎች የገበያ ትስስር፣ ንግድን ለማስፋፋትና የፋይናንስ አቅማቸውን ለማጠናከር ትልቅ እድል እንደሚፈጥር ሚኒስትር ዴኤታዋ ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ሴት ነጋዴዎችን ለማጠናከር በትኩረት እየሠራች ነው ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
ማውሪን ሱምብዌ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ የንግድ ኤግዚቢሽንና ኮንፈረንሱን ለማካሄድ ምቹ ሁኔታ አላት ብለዋል፡፡