Fana: At a Speed of Life!

የልማት ፕሮጀክቶችን ተደራሽ ለማድረግ መሥራት ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የልማት ፕሮጀክቶችን በሁሉም አካባቢዎች በፍትሐዊነት ተደራሽ ለማድረግ መሥራት እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

በክልሉ በመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሂዷል፡፡

በዚሁ ወቅት እያደገ የመጣውን የሕዝብ ፍላጎት ለማሟላት በፕሮጀክት አሥተዳደር ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን አስቀድሞ መፍታት እንደሚገባ ርዕሰ መሥተዳድሩ አስገንዝበዋል፡፡

የተጀመሩ የመንገድ ግንባታዎችን በፍጥነት ከማጠናቀቅ አንጻር ያለውን ውስንነት መፍታት እንደሚገባም አስረድተዋል፡፡

ከኮሪደር ልማት ሥራ ጋር በተያያዘም በተመረጡ አራት ከተሞች እየተከናወነ ያለው ሥራ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንዲጠናቀቅ ማሳሰባቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽንቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር ዋና ዳይሬክተር መሀመድ አብዱረህማን (ኢ/ር) በበኩላቸው፤ የተጀመሩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ በትኩረት መሥራት ይገባል ብለዋል፡፡

የመንገድ መሰረተ ልማት ፍላጎት የሁሉንም አካላት የተቀናጀ ጥረት እንደሚጠይቅ ጠቁመው፤ በመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አፈጻጸም ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ጉዳዮችን መለየት እንደሚገባ አመላክተዋል።

የፕሮጀክት አሥተዳደር ዐቅምን በማሳደግ ለውጤታማነቱ መሥራት እንደሚገባም አንስተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.