ኢትዮ ቴሌኮም የተለያዩ ሽልማቶችን የሚያስገኝ ዕጣ አወጣ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም የኤሌክትሪክ መኪናን ጨምሮ ሌሎች ምርቶችን ለደንበኞቹ የሚሸልምበት ዕጣ የማውጣት ሥነ-ሥርዓት አከናወነ።
ኢትዮ ቴሌኮም የተቋቋመበትን 130ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ነው የኤሌክትሪክ መኪናን ጨምሮ በርካታ ሽልማቶችን ያዘጋጀው።
በዚህ መሰረት ለደንበኞቹ ሽልማት በማዘጋጀት በዕጣ ሲሸልም በአምስት ወራት ውስጥ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ተነግሯል።
በዛሬው የዕጣ ማውጣት ሥነ-ሥርዓት ሁለት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችና አምስት ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች (ሶስት በኤሌክትሪክ ሁለት በነዳጅ የሚሰሩ) ለዕድለኞች ይፋ ተደርገዋል።
በአሸናፊ ሽብሩ