Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ባህር ዳር በሰፋፊ መንገዶች እየተዋበች መሆኗን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባሕር ዳር ከተማ ኅብረተሰቡ በሚዝናናባቸው መናፈሻዎች፣ ብስክሌት በነጻነት ማሽከርከር በሚያስችሉ ሰፋፊ መንገዶች እየተዋበች ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ÷ ጣናን ከልሎ የነበረው ጢሻ ተገላልጦ የሐይቁ ድብቅ ውበት ፍንትው ብሎ መመልከት ሀሴትን ያጎናፅፋል ብለዋል፡፡

ለአገልግሎት ክፍት የሆኑትም ሆነ በሂደት ላይ የሚገኙ የህዝብ መዝናኛ ስፍራዎች፣ በዘላቂነት ለረጅም ዓመታት እንዲያገለግሉ ኅብረተሰቡ በባለቤትነት መንፈስ ሊጠብቃቸው እና ሊንከባከባቸው እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.