Fana: At a Speed of Life!

ድርጅቶቹ ለክትባት ተደራሽነት ድጋፋቸውን እንደሚያጠናክሩ አረጋገጡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ለክትባት ተደራሽነትና የህጻናት ሥርዓተ ምግብን ለማሻሻል የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የተለያዩ ግብረሰናይ ድርጅቶች ገልጸዋል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ከዩኒሴፍ፣ ከጋቪ የክትባት ተቋምና ከሲ አይ ኤፍ ኤፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በክትባት ተደራሽነትና የህጻናት የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን ለመቅረፍ በቅንጅት እየተሰሩ ባሉ ሥራዎች ዙሪያ መክረዋል።

በመደበኛው የክትባት መርሐ-ግብር ክትባት ያላገኙና ጀምረው ያቋረጡ ህጻናትን በማካካሻ ክትባት ተደራሽ ለማድረግ ግብረ-ሐይል ተቋቁሞ እየተሠራ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል፡፡

የግብረሰናይ ድርጅቶቹ የሥራ ኃላፊዎች በበኩላቸው÷ የክትባት ተደራሽነትንና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ችግርን ለመፍታት እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ለዘርፉ ውጤታማነት የሚያደርጉትን የቁሳቁስና የፋይናንስ ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ማረጋገጣቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.