Fana: At a Speed of Life!

የሶማሊያ ካቢኔ የኢጋድ የማቋቋሚያ ስምምነትን ለሀገሪቱ ፓርላማ መራ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሶማሊያ መንግስት ካቢኔ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ማቋቋሚያ ስምምነትን በመደገፍ በሀገሪቱ ፓርላማ እንዲጸድቅ መምራቱ ተገልጿል፡፡

ኢጋድ የሶማሊያ ካቢኔን ውሳኔ ተከትሎ ባወጣው መግለጫ÷ ውሳኔው ለቀጣናው ትብብርና እድገት ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን አመልክቷል፡፡

የሶማሊያ ካቢኔ የተሻሻለውን የኢጋድ ስምምነት ማጽደቁ ሀገሪቱ በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም ልማትን ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነውም ብሏል።

ኢትዮጵያን ጨምሮ የተሻሻለውን የኢጋድ የማቋቋሚያ ስምምነት ያፀደቁ ሀገራት ለቀጣናው ትብብር ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያመላክት ነው ሲልም ኢጋድ በመግለጫው ጠቁሟል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.