Fana: At a Speed of Life!

ወላይታ ድቻ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ21ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ወላይታ ድቻ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ለወላይታ ድቻ ብቸኛዋን የማሸነፊያ ግብ አብነት ደምሴ አስቆጥሯል።

ፈረሰኞቹ ሶስተኛ ተከታታይ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ወላይታ ድቻ በ30 ነጥብ 6ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ29 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በጨዋታው ከረጅም ጊዜ የጉዳት ቆይታ በኋላ ወደ ሜዳ ተመልሶ የነበረው የወላይታ ድቻው ተጨዋች መልካሙ ቦጋለ በዛሬው ጨዋታም ጉዳት አጋጥሞት ተቀይሮ ለመውጣት ተገድዷል።

ቀደም ብሎ ቀን 9፡00 ላይ በተካሄደው የሊጉ መርሐ-ግብር ፋሲል ከነማ እና ባህር ዳር ከተማ በአቻ ውጤት ተለያይተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.