Fana: At a Speed of Life!

ለአፍሪካ ተገቢውን ቦታ ያልሰጠ ዓለም ውጤት አያመጣም- ቻይና

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቻይና አፍሪካ በዓለም የኃይል አሰላለፍ ተገቢው ቦታ እንዲኖራት ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋገጠች፡፡

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በሰጡት መግለጫ፤ አዳጊ ሀገራት በዓለም አቀፍ ተቋማት ተገቢው ውክልና እንዲኖራቸው የተጀመሩ ሥራዎችን ማስቀጠል አለባቸው ብለዋል፡፡

የቻይና አፍሪካ የትብብር መድረክ ፎካክ ዘንድሮ 25ኛ ዓመቱን እንደሚይዝ ጠቅሰው፤ በእነዚህ ዓመታት በርካታ ስኬቶች መገኘታቸውን አንስተዋል፡፡

በተለይም በመሠረተ-ልማትና በኢኮኖሚ ጠንካራ ውጤቶች ተገኝተዋል ማለታቸውን ቻይና ዴይሊ ዘግቧል፡፡
በ21ኛው ክፍለ ዘመን ዓለም ለአፍሪካ ተገቢውን ቦታ ሳይሰጥ የሚፈለገውን ውጤት አያመጣም ሲሉም በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም የተጀመሩ የዓለም አቀፍ ተቋማት ማሻሻያ ሥራዎች ይህን ታሳቢ ማድረግ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

አፍሪካ የመጪው ዓለም ወሳኝ መሆኗን ጠቅሰው፤ አኅጉሪቱን በመሠረተ-ልማት ከማስተሳሰር ባለፈ የምግብ ዋስትናዋን እንድታረጋግጥ ቻይና ድጋፏን ትቀጥላለች ብለዋል፡፡

አያይዘውም ሀገራቸው በዩክሬንና መካከለኛው ምሥራቅ ያሉ ግጭች በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲፈቱ እንደምትፈልግ አስረድተዋል፡፡

የቻይና አፍሪካ ጉባዔ የሁለቱን ግንኙነት ለማጠናከር መሠረት የሚጣልበት መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.