Fana: At a Speed of Life!

በፕሬዚዳንት ትራምፕ የፖሊስ ኦፊሰርነት ሹመት የተሰጠው የካንሰር ታማሚ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለ13 ዓመቱ የካንስር ታማሚ ታዳጊ የፖሊስ ኦፊሰርነት ሹመት በመስጠት የልጅነት ህልሙ እውን እንዲሆን ማድረጋቸው የዓለምን ትኩረት ስቧል፡፡

ዲጄ ዳንኤል የተባለው የ13 ዓመት ታዳጊ ህልሙ የፖሊስ ባለሙያነት ቢሆንም፤ ከ2018 ጀምሮ ባጋጠመው የብሬን ካንሰር ህመም ምከንያት ሰባት ዓመታትን ከህመሙ ጋር በመታገል አሳልፏል፡፡

ለመሞት አምስት ወራት ብቻ እንደቀረው በዶክተሮቹ የተነገረው ታዳጊው፤ በመጨረሻዎቹ ሰዓታት የልጀነት ህልሙ እውን የሚሆንበት የፖሊስ ባሉሙያነት ሥራ በፕሬዚዳንት ትራምፕ ተሳክቷል፡፡

ትራምፕ ከሰሞኑ በአሜሪካ ኮንግረስ የጋራ ስብሰባ ላይ ንግግር ባደረጉበት ወቅት÷ ዲጄ ዳንኤል የአሜሪካ ሴክሬት ሰርቪስ አባል እንዲሆን ሹመት ሰጥተዋል፡፡

የኮንግረስ አባላትም በዕለቱ የዶናልድ ትራምፕን ውሳኔ በማድነቅ እና ለታዳጊው ድጋፋቸውን ለማሳየት ከ30 ሰከንድ በላይ የቆየ ጭብጨባ በአዳራሹ ውስጥ አሰምተዋል፡፡

በስብሰባው የአሜሪካ ሆስቲን ፖሊስ ዩኒፎርም በመልበስ አዳራሽ ውስጥ የተገኘው ዲጄ ዳንኤል÷ ከወላጅ አባቱ ጋር በመሆን በተሰጠው ሹመት እና የህልሙ መሳካት በደስታ ሲያነባ የታየበትን ምስል የዓለም መገናኛ ብዙኃን አጋርተውታል፡፡

ከጥቁር አሜሪካዊ ቤተሰቦች የተገኘው ዲጄ ዳንኤል በሚቀጥሉት ጊዜያት የአሜሪካ ሴክሬት ሰርቪስ አባል በመሆን ሥራውን ይጀምራል ተብሏል፡፡ ይህም በካንሰር ለሚሰቃዩ ሰዎች ተስፋን የሰጠ ነው መባሉን ሲኤን ኤን ዘግቧል፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.