Fana: At a Speed of Life!

የተቋማትን የሳይበር ደኅንነት ለማስጠበቅ …

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) መንግሥታዊም ሆኑ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት የሳይበር ደኅንነታቸውን ለማስጠበቅ የተለያዩ ፕሮግራሞችን መቅረጽና መተግበር ዋና ተግባራቸው ሊሆን እንደሚገባ ይመከራል፡፡

በዚህም የተቋማቱ የሳይበር ደኅንነት ፕሮግራም የተቀናጀና የሚከተሉት ዋና ዋና መፍትሔዎችን ያካተት ሊሆን እንደሚገባ ኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት መረጃ ያመላክታል፡፡

👉 የሥጋት ዳሰሳ እና ኦዲት ማድረግ፤

👉 ወቅቱን በጠበቀ መልኩ የሳይበር ደኅንነት ሥጋት ዳሰሳና ኦዲት ማከናወን፤

👉 ሥጋትን መሠረት ባደረገ መልኩ መፍትሔዎችን መለየት፤

👉 ንቃተ ኅሊና መገንባት፤

👉 የሠራተኞችንና የባለድርሻ አካላትን የሳይበር ደኅንነት ንቃተ ኅሊና ደረጃ መገምገም፤

👉 ቀጣይነት ያለው የሳይበር ደኅንነት ንቃተ ኅሊና ስልጠና እና ሌሎች መርሐ-ግብሮች ማዘጋጀት፤

👉 የአመራርና አሥተዳደር መፍትሔዎችን ማዘጋጀት፤

👉 የሳይበር ደኅንነት ስትራቴጂ፣ ፖሊሲዎችና መመሪያዎች እንዲሁም የሥራ ሂደቶችን ማዘጋጀትና መተግበር፤

👉 ሀገራዊና ሌሎች አስፈላጊ የሳይበር ደኅንነት ስታንዳርዶችን መተግበር፤

👉 አደረጃጀት መፍጠርና ዐቅም መገንባት፤

👉 የሳይበር ደኅንነት የሥራ ክፍል ማደራጀት፤

👉 የሳይበር ደኅንነት ባለሙያዎችን መመደብና በቀጣይነት ዐቅማቸውን መገንባት፤

👉 ቴክኖሎጂያዊ መፍትሔዎችን መተግበር፤

👉 ሁሉንም የመረጃ ሀብቶችና ሥርዓቶች መጠበቅ የሚያስችሉ ቴክኖሎጂያዊ መፍትሔዎችን ማስቀመጥና ማዘመን፤

👉 የሳይበር ደኅንነት ኦፕሬሽን ማዕከል መገንባት፤

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.