ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከሬቨረንድ ፍራንክሊን ግራሃም ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከቢሊ ግራሃም ኢቫንጀሊካል አሶሴሽን ፕሬዚዳንት ሬቨረንድ ፍራንክሊን ግራሃም ጋር ተወያይተዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ሬቨረንድ ፍራንክሊን ግራሃምን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው እንኳን ደህና መጡ ማለታቸውን ገልጸዋል፡፡
ፍራንክሊን ግራሃም እንደ አባታቸው ሁሉ ለኢትዮጵያ ጥልቅ ፍቅር ያላቸው መሆኑን እንደገለጹና ሁሌ እንደሚፀልዩ እና ላለፉት 40 ዓመታት ኢትዮጵያን በተደጋጋሚ እንደጎበኙ ጠቅሰዋል።
ሬቨረንድ ፍራንክሊን ግራሃም በአዲስ አበባ ከተማ ባዩት ፈጣን ለውጥ መደነቃቸውን አመልክተዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች ሬቨረንድ ፍራንክሊን ግራሃም ለኢትዮጵያ እና ህዝቦቿ ላሳዩት ፍቅር እና መልካም ምኞት አመስግነዋል።