ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታውን ያደርጋል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታውን ከካሜሩን ብሔራዊ ቡድን ጋር ያከናውናል።
የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ ፤ በኦሌምቤ ስታዲየም ምሽት 3 ሠዓት ላይ ይደረጋል፡፡
በዚህ ጨዋታ ላይ ኢትዮጵያ ሙሉ ቢጫ መለያ እንደምትጠቀም መገለጹን የእግር ኳስ ፌደሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡