Fana: At a Speed of Life!

939 ሚሊየን ብር ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን ከየካቲት 21 እስከ 27 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 939 ሚሊየን ብር ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶቹ በኩል መያዙን አስታወቀ፡፡

ከተያዙት ዕቃዎች መካከልም፤ ማዕድናት፣ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ ጥራጥሬ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ ዕቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ መድኃኒት፣ የቁም እንስሳት እና የውጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል ብሏል፡፡

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የገቢ እና የወጭ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር፤ ሞያሌ፣ አዋሽ እና አዲስ አበባ ኤርፖርት ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ መያዛቸውን በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.