Fana: At a Speed of Life!

አገልግሎቱ ምንም አይነት አዲስ የታሪፍ ማሻሻያ አለመደረጉን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሚያዝያ ወር ጀምሮ አዲስ የታሪፍ ማሻሻያ ተግባራዊ ሊደረግ ነው በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሃሰተኛ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ስለሆነም ከሚያዝያ ወር ጀምሮ የሚደረግ አዲስ የታሪፍ ማሻሻያ አለመኖሩን ነው ተቋሙ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ ያረጋገጠው፡፡

ከመስከረም 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ4 ተከታታይ ዓመታት በማኅበረሰቡ ላይ ጫና እንዳይፈጠር በየሩብ ዓመቱ ተከፍሎ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘውን የታሪፍ ማስተካከያ ከማስፈጸም ውጪ አዲስ የታሪፍ ማሻሻያ አለመኖሩንም አመልክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.