Fana: At a Speed of Life!

397 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲና ኦማን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያና ኦማን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 397 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

255 ወንዶች፣ 40 ሴቶች እና 18 ጨቅላ ሕጻናት በድምሩ 313 ኢትዮጵያውያን በተያዘው ሳምንት ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ከተመላሾች መካከል 75 ዕድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙ ተመላክቷል፡፡

በተመሳሳይ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 83 ወንዶች እና 1 ሴት ኢትዮጵያውያን ከኦማን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ነው የተገለጸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.