Fana: At a Speed of Life!

ቼልሲ ሌስተር ሲቲን በማሸነፍ ደረጃውን አሻሻለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ28ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቼልሲ በሜዳው ስታምፎርድ ብሪጅ ሌስተር ሲቲን አስተናግዶ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ለምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ብቸኛዋን የማሸነፊያ ግብ ማርክ ኩኩሬላ በ60ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡

ባለ ሜዳው ቡድን ቼልሲ በመጀመሪያው አጋማሽ ፍፁም ቅጣት ምት አግኝተው ሳይጠቀምበት የቀረው እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጫዋች ኮል ፓልመር በፕሮፌሽናል እግር ኳስ ሕይወቱ ለጀመሪያ ጊዜ የፍፁም ቅጣት ምት ስቷል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ቼልሲ በ49 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሌስተር ሲቲ በ17 ነጥብ ወራጅ ቀጠና 19ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ በሌላ የሊጉ መርሐ ግብር ቦርንማውዝ እና ቶትንሃም ያደረጉት ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡

ለቦርንማውዝ ታቨርነር እና ኢቫኒልሰን ግቦቹን ሲያስቆጥሩ ለቶትንሃም ደግሞ የአቻነት ግቦቹን ሳር በጨዋታ እንዲሁም ሰን በፍፁም ቅጣት ምት ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

የዕለቱ ተጠባቂ ጨዋታ ምሽት 1 ሰዓት ከ 30 ሲል በኦልድትራፎርድ ስታዲየም ማንቼስተር ዩናይትድን ከአርሰናል ያገናኛል፡፡

የማንቼስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ከአርሰናል ጨዋታ በፊት በክለቡ ስታዲየም አቅራቢያ የክለቡ ባለቤቶች ላይ ተቃውሟቸውን እያሰሙ ይገኛሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.