Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል 8 ነጥብ 8 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ ታቅዷል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለ2017/18 የምርት ዘመን 8 ነጥብ 8 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ መታቀዱን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታውቋል።

በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ሃላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) ÷በክልሉ በምርት ዘመኑ ከ5 ነጥብ 4 ሚሊየን ሄክታር መሬት ለማረስ መታቀዱን ገልጸዋል።

ከሚታረሰው መሬት 186 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት መታቀዱን ጠቁመው÷ለምርቱ ውጤታማነት 8 ነጥብ 8 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ እየተሠራ ነው ብለዋል።

ከትራንስፖርት ዋጋ እና የዶላር ምንዛሬ ጭማሪ ጋር ተያይዞ የዘንድሮው የአፈር ማዳበሪያ መሸጫ ዋጋ ጭማሪ ማሳየቱን ያነሱት ሃላፊው÷የአርሶ አደሮች የመግዛት አቅም እንዲጨምር ከ80 ቢሊየን ብር በላይ መንግሥት ድጎማ ማደረጉን ተናግረዋል፡፡

እስካሁን ከ350 ሺህ በላይ ለሚሆኑ አርሶ አደሮች ታች ድረስ በመውረድ በማዳበሪያ አጠቃቀም እና በዋጋ ጭማሪው ላይ ውይይት መደረጉን ነው ያብራሩት፡፡

በሥርጭት ሒደቱ ችግር እንዳይፈጠር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መግባባት ላይ እንደተደረሰ መግለጻቸውንም አሚኮ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.