በደንዲ ወረዳ በትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ደንዲ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የስድስት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
አደጋው ከግንደበረት ወረዳ ወደ ጊንጪ ከተማ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በመገልበጡ ነው የተከሰተው፡፡
በደረሰው አደጋም የ6 ሰዎች ሕይወት ማለፉንና በ16 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የወረዳው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በጊንጪ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሕክምና እየተከታተሉ ሲሆን÷የአደጋው መንስኤም እየተጣራ ነው ተብሏል፡፡