ባሕር ዳር ከተማ ሀዲያ ሆሳዕናን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት1፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ22ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ባሕር ዳር ከተማ ሀዲያ ሆሳዕናን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የባሕር ዳር ከተማን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ፍቅረሚካኤል ዓለሙ በ90ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ አሳርፏል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ባሕር ዳር ከተማ በ33 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ በሊጉ ሶስት ተከታታይ ጨዋታዎች ድል ያልቀናው ሀዲያ ሆሳዕና በ32 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል ምሽት 12 ሰዓት ላይ ሲዳማ ቡና ከአዳማ ከተማ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡