Fana: At a Speed of Life!

የአፋርና ሶማሌ ክልል ርዕስ መስተዳድሮች በተገኙበት በጅግጅጋ የኢፍጣር መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፋር እና ሶማሌ ወንድማማች ህዝቦች ታላቅ የጋራ የኢፍጣር መርሐ ግብር በጅግጅጋ እየተካሄደ ነው።

በመርሐ ግብሩ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፣ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ፣ የሰላም ሚኒስትር መሃመድ ኢድሪስ እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ ተገኝተዋል።

እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች እና የፌደራል መንግስት ተቋማት ሃላፊዎች በመርሐ ግብሩ መታደማቸው ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.