Fana: At a Speed of Life!

የካፍ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ በካይሮ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ በግብጽ ካይሮ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ከዋናው ጉባዔ አስቀድሞ የሚካሄደው የክፍለ አህጉር ማህበራት ስብሰባ በዛሬው ዕለት የካፍ ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሞሴፔ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል።

በነገው ዕለት የካፍ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ የሚከናወን ሲሆን÷የፊታችን ረቡዕ ደግሞ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት እና የካፍ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ኢሳያስ ጅራ፣  ምክትል ፕሬዝዳንት ዳኛቸው ንግሩ (ዶ/ር) እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ባሕሩ ጥላሁን በጉባዔው እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

የካፍ 46ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ባሳለፍነው ጥቅምት ወር በአዲስ አበባ ላይ መካሄዱ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.