Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ መድን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ

‎አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ22ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መሐ-ግብር ኢትዮጵያ መድን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የኢትዮጵያ መድንን የማሸነፊያ ግቦች አለን ካይዋ እና አቡበከር ሳኒ ሲያስቆጥሩ፤ ንግድ ባንክን ከሽንፈት ያልታደገች ብቸኛ ግብ ኪቲካ ጅማ ከመረብ አሳርፏል፡፡

ሁለተኛ ተከታታይ ድሉን ያሳካው ኢትዮጵያ መድን በ41 ነጥብ የሊጉን መሪነት አጠናክሮ ሲቀጥል፥ ሽንፈት ያስተናገደው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ28 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

የሊጉ መርሐ-ግብር ሲቀጥል ምሽት 12 ሰዓት ላይ ወላይታ ድቻ ከ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.