ሐዋሳን ልዩ ውበት የሚያላብስ የኮሪደር ልማት እየተሠራ ነው – አቶ ደስታ ሌዳሞ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለሐዋሳ ከተማ ልዩ ውበት የሚያላብስ የኮሪደር ልማት እየተሠራ እንደሚገኝ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ደስታ ሌዳሞ ገልጸዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በሐዋሳ ከተማ እየተሠራ የሚገኘውን የቀጣይ ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ሥራ ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸውም ወቅት÷ የኮሪደር ልማት ሥራው 12 ኪሎ ሜትር ርዝመት እንዳለውና ሲጠናቀቅም ለሀዋሳ ልዩ ውበት የሚያላብስ እንደሆነ ተናግረዋል።
የኮሪደር ልማቱ የአስፋልት፣ የእግር መንገድ፣ የሕዝብ መዝናኛ፣ የመኪና፣ የታክሲና አውቶብስ ተርሚናሎችን፣ የብስክሌት መንገድ እንዲሁም በሀይቁ አካባቢ በርካታ የልማት ሥራዎች እንደሚሰሩበት ገልጸዋል።
ብዙዎች ለጉብኝት መርጠው የሚመጡበት ከተማ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ መሆኑንም አመልክተዋል።
የዚህ ምዕራፍ የሀዋሳ ከተማ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት እስከ ሰኔ ወር እንደሚጠናቀቅ የገለጹት አቶ ደስታ÷ በዕቅዱ መሠረት መንግሠት ሥራዎችን በልዩ ድጋፍና ክትትል እየሠራ እንደሚገኝ መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።