Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በጅግጅጋ ከተማ የጎርፍ ውሃ ማፋሰሻ ግንባታ የሥራ ሂደትን ጎበኙ

‎አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ የጅግጅጋ ከተማ የጎርፍ ውሃ ማፋሰሻ ግንባታ የሥራ ሂደትን ጎብኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በጅግጅጋ ከተማ በዝናብ ወቅት የሚከሰተውን ጎርፍ ለመከላከል እየተሰራ የሚገኘውን የጎርፍ ውሃ ለመቆጣጠር እና ለማስተዳደር የውሃ ማፋሰሻ ሥራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

ፕሮጀክቱ በጅግጅጋ ከተማ በተለይም በዝናብ ወቅት የሚከሰተውን ጎርፍ ለመከላከል እንደሚያስችል ተገልጿል።

ፕሮጀክቱ በአሁኑ ጊዜ በመጠናቀቅ ደረጃ ላይ እንደሚገኝም የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ኤጄንሲ መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.