Fana: At a Speed of Life!

የብሄራዊ ድህረ-ምረቃ የፈተና መስጫ ቀን ተራዘመ

‎አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሶስተኛው ብሄራዊ ድህረ-ምረቃ (NGAT) የፈተና መስጫ ቀን ወደ መጋቢት 12 ቀን 2017 ዓ.ም መዘዋወሩን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ፈተናው መጋቢት 5 እንዲሰጥ ቀን ተቆርጦለት እንደነበር ያስታወሰው ሚኒስቴሩ÷ አንዳንድ ተፈታኞች ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ፈተናው ወደ መጋቢት 12 መራዘሙን አስታውቋል።

መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም የተጠናቀቀው የአመልካቾች ምዝገባም እስከ መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት 12 መራዘሙንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

በተለያየ ምክንያት ምዝገባ ያመለጣቸው አመልካቾች ምዝገባቸውን በተሰጠው ቀነ ገደብ ውስጥ እንዲያጠናቅቁም ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.