ዓባይ ባንክ ለመቄዶንያ የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዓባይ ባንክ ለመቄዶንያ የአረጋዊያን እና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
ባንኩ ለማዕከሉ እየተካሄደ በሚገኘው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ ነው ድጋፉን ያበረከተው።
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የኋላ ገሠሠ በዚህ ወቅት÷ ዓባይ ባንክ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ባስቀመጠው ተቋማዊ መርህ መሠረት የዜጎችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ዘርፈ ብዙ ድጋፎች በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በዛሬው ዕለት ለመቄዶንያ የአረጋዊያን እና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የተደረገው የገንዘብ ድጋፍም የዚህ አካል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
መቄዶንያ እያከናወነ የሚገኘው የበጎ አድራጎት ሥራ የሚበረታታ መሆኑን አንስተው÷ በቀጣይም ባንኩ መሰል ድጋፎችን እንደሚያደርግ መናገራቸውን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።