ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ በጎዴ የተገነባውን የኮር ጠቅላይ መምሪያ ካምፕ መርቀው ከፈቱ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በሶማሌ ክልል ጎዴ የተገነባውን የመከላከያ ሠራዊት የኮር ጠቅላይ መምሪያ ካምፕ መርቀው ከፍተዋል።
የኮሩ ጠቅላይ መምሪያ በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ተገንብቶ የተጠናቀቀ ሲሆን፥ የሠራዊቱን አኗኗር የሚያዘምን እንዲሁም የግዳጅ አፈጻጸሙን የሚያተልቅ አስፈላጊ መሰረተ-ልማት የተሟላለት መሆኑ ተገልጿል።
በመርሐ-ግብሩ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የማዕድን ሚኒስትር ሃብታሙ ተገኝን (ኢ/ር) ጨምሮ የመከላከያ እና የሶማሌ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በኮር ጠቅላይ መምሪያው ከ40 ዓመት በፊት በ1968 ዓ.ም የነበረው የሻለቃ ካምፕ፤ ወደ ኮር ጠቅላይ መመሪያ ካምፕ ማደጉን የሚያበስር የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።
በተጨማሪም የችግኝ ተከላ ፕሮግራም መከናወኑን ከመከላከያ ሰራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።