Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሐረር የልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሐረር የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸውም፤ ለክልሉ ኮሪደር ፕሮጀክቶች በሀገር ውስጥ የተሰሩ ቁሳቁስ የሚያመርተውን የማስ ኢንጂነሪንግ ኢንተርፕራይዝ እና የሌማት ትሩፋት ማሳያ ተመልክተዋል።

በተጨማሪም ለክልሉ በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የተገነባውን የዳቦ ፋብሪካ ተዘዋውረው መመልከታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.