Fana: At a Speed of Life!

የአርባምንጭ ስታዲየም ግንባታ በ4 ነጥብ 32 ቢሊየን ብር ወጪ እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአርባምንጭ ስታዲየም ግንባታ በ4 ነጥብ 32 ቢሊየን ብር ወጪ እየተከናወነ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ኦላዶ ኦሎ ገለጹ፡፡

ግንባታውን በሁለት ዓመታት ውስጥ ለማጠናቀቅ ውል መገባቱን አውስተዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በፈረንጆቹ ሐምሌ 28 ቀን 2024 መጀመሩን ገልጸው፤ እስከ አሳለፍነው የካቲት ወር ድረስ አፈጻጸሙ 13 ነጥብ 1 በመቶ መድረሱን ለፋና ዲጂታል አረጋግጠዋል፡፡

በዚህ ሂደት ውስጥ እንደ ሲሚንቶ እና የተፈጥሮ አሸዋ የመሳሰሉት የግንባታ ዕቃዎች አቅርቦት ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶች አሉታዊ ጫና ማሳደራቸውንም አንስተዋል፡፡

ስታዲየሙ በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማኅበር የበላይ ጠባቂ (ፊፋ) ስታንዳርድ መሠረት እየተገነባ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ግንባታው እየተከናወነ ያለው በሕብረተሰብ ተሳትፎ፣ በመንግሥት እና በልማት አጋሮች ድጋፍ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

የስታዲየሙ ግንባታ ሲጠናቀቅ፤ እንደ ሀገር በዘርፉ ያለውን ችግር ለመቅረፍ በሚደረገው ጥረት የራሱን በጎ ዐሻራ እንደሚያኖር አመላክተዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.