Fana: At a Speed of Life!

ለመድሃኒትና ሕክምና ግብዓት ግዢ 12 ቢሊየን ብር በጀት መያዙ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከ12 ቢሊየን ብር በላይ በጀት በመመደብ የመድሃኒት እና የሕክምና ግብዓት ግዢ ለመፈጸም ዝግጅት መደረጉን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የጤና ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ 5 ሺህ የጤና ዘርፍ ሃላፊዎች እና ባለ ድርሻ አካላት ጋር እየመከረ ነው፡፡

በመድረኩም በሕክምና ግብዓት አቅርቦት እና ተደራሽነት እንዲሁም በመረጃ አያያዝ እና አጠቃቀም ዙሪያ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በዚህ ወቅት÷ከመድሃኒት እና ግብዓት አቅርቦት ጋር ተያይዞ የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ ከ12 ቢሊየን ብር በላይ በጀት መያዙን አንስተዋል።

የመድሃኒት እና ግብዓት አቅርቦት ወሳኝ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሯ÷በቀጣይ ችግሮችን ለመቅረፍ በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡

ባለድርሻ አካላትም በዘርፉ የሚያደርጉትን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡፡

በእሸቱ ወ/ሚካኤል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.