ፋሲል ከነማ መቻልን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ22ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ መቻልን 4 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
በጨዋታው ለፋሲል ከነማ ጌታነህ ከበደ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር÷ ቀሪዎቹን ደግሞ ቢኒያም ጌታቸው እና ምኞት ደበበ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
መቻልን ከሽንፈት ያልታደጉትን ሁለት ግቦች አቤል ነጋሽ እና ፊሊሞን ገብረፃዲቅ አስቆጥረዋል፡፡
በሊጉ ከሶስት ተከታታይ ጨዋታዎች በኃላ ወደ ድል የተመለሰው ፋሲል ከነማ በ27 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ መቻል በ29 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል ምሽት 12 ሰዓት ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከድሬዳዋ ከተማ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡